=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እናት ሐግራችን ኢትዮጲያ ብዙ አንባገነኖችን ከጥንት ጀምሮ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ እያስተናገደች ትገኛለች። በጥንት ጊዜ የነበሩ አምባገነኖች በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ እራሳቸውን ልክ እንደ ፈጣሪ ወይም ደግሞ ከፈጣሪ ዘንድ እንደተሾሙ አድርገው ሲያቀርቡልን ኑረዋል። ይህን ያደርጉበት የነበርው ዋነኛው ምክኒያት በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራቸውና ህዝቡ ሳይወድ በግድ በነሱ አስተዳደር ውስጥ እንዲሆን ነበር። አሁን ያሉ አምባገነኖችም ቅርፃቸውን ቀይረው የህገመንግስት የበላይነት የሚል መፈክር አንግበው እንደፈለጉ በሚተረጉሙትና በሚሽሩት ህገመንግስት ህዝቡን ከጫማቸው ስር ማድረግ ይሻሉ። ታዲያ ዱሮ የነበሩትንም ሆነ አሁን ያሉትን አንባግነኖች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር በኢስላም ላይ የዘመቱ የጥፋት ሃይሎች መሆናቸው ነው።
በአፄዎቹ ዘመን የነበሩ አንባገነኖች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የረጅም ጊዜ እምነትንም ሆነ ህዝብን የማጥፋት ጦርንት አውጀው ነበር። ከነዚህም መካከል አፄ ሚኒልክ እና አፄ ዩሓንስ ይጠቀሳሉ። በ1870 አፄ ዩሓንስ ወሎ ቦሩ ሜዳ አካባቢ የኦርቶዶክስ እምነት አባቶችን ብቻ ሰብስቦ ከተማከረ ቡኋላ ከኦርቶዶክስ እምነት ውጭ እምነት እንደሌለና የሌሎች እምነት መሪዎች ከሐገር እንዲሰደዱ ፣ ሙስሊሞች ክርስትናን በሃይል እንዲንዲቀበሉ እንዲሁም ይህን አሻፈረኝ የሚሉ እንደሚቀጡ ጭምር አወጀ። ከታሪካችን እንደምንረዳው ይህን የረጅም ጊዜ እምነትንም ሆነ ህዝብን የማጥፋት ጦርነት ያወጁት አፄዎች ብቻ አልነበሩም ከአፄዎቹና ከንጉሶቹ ጀረባ የነበሩት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናቶችና ፓፓሶች ጭምር እንጅ!
ታዲ ያኔ የወሎ ሙስሊሞች እምነታቸውን ቀይረው እንዲኖሩ ፣ የክርስቲያን ስጋ ሳይወዱ በግዱ እንዲበሉ ፣ መስቀል እንዲነቀሱ ያደርጉ የነበረ ሲሆን ይህን አሻፈረኝ ያሉ ብዙ ሙስሊሞችን ገለዋል ፣ የከፋ እንግልትና በደል አድርሰውባቸዋል ፣ ቀያቸውንም ለቀው እንዲሰደዱ ተደርጎል። ይሁንእንጅ ይህን ጦርነት ያወጁት በየጁ ወይም በወሎ ሙስሊሞች ላይ ብቻ አልነበረም። የሃገሪቱን ግዛት በማስፋፋት ዘመቻ ላይ በደቡብ ፣ በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሚገኙ ሙስሊሞችም ተመሳሳይ እጣፋንታ ገጥሟቸዋል። አስቡት ይህን በደል እና ግፍ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ሲፈፅሙ ኑረው ነው ዛሬ ክሪስቲያኑና ሙስሊሙ ተዋዶ የሚኖሩባት ሃገር፤ የሽ አመት ጎረቤቶች እያሉ የሚደሰኩረት። ኢሃዲግ ይህን እያለ የሚደሰኩረው ለምንም አይደለም የረጅም ጊዜ የስልጣን ጥማቱን ለማርካት እንጅ።
የደደቢት ነፍጠኛ የሆነው ኢሃዲድ ከአፄዎቹ ኢስላምን የማጥፋት ዘመቻ ወርሶ ትግሉን ሀ ብሎ ከጀመረ ሰነባብቷል። ይህ ዘመቻ ከአፄዎቹ ዘመቻ ባካሄድ የተለያና የረቀቀ ሲሆን ኢስላምንም ሆነ ሐገርን የማጥፋት ዘመቻ ነው። ድሮ የነበሩ አፄዎች አይን ያወጣ ትግል ማለትም ህዝብን የመግደል እና የማሰደድ ፣ በሃይል እምነትን የማስቀየር ጦርነት ሲሆን አሁን ያሉ አፄዎች ግን እምነትን የመበረዝ ፣ የሃይማኖት አባቶችን የማሰደድና የማሰር ፣ የሙስሊሞች ተቋማትን የመዝጋት ፣ ሙስሊም ተማሪዎችን በትምህርቱ ዘርፍ ወደኋላ የማስቀረት ዘመቻ ነው።
እነዚህን አፄዎች መብቴ ተነፍጓል ፍትህ እጠይቃለሁ ያላቸውን ፣ በሐገራዊ ጉዳይ ላይ የተቻቸውን ፣ ሚስጥራቸውን ያጋለጠባቸውን ሰው አንድም እድሜልኩን ተፈርዶበት እስርቤት እንዲማቅቅ አልያም ለገዥው ድርጅት አስጊነው ተብሎ ከታሰበም እንዲገደል እና መብቴ ይከበርልኝ ብሎ የወጣውንም ህዝብ ለጭፍጨፋ እና ለእንግልት ሲዳርጉት ይታያል። ይህን ሁሉ ቢያደርጉም ከከንቱ ልፋትነት አይዘልም!!!
አሏሁ አዘወጀል በቀርአኑ በሱረቱ ተውባ አንቀፅ 32 ላይ እንዲህ ይላል፦
=<({አል-ቁርአን 9:32})>=
{32} የአሏህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉት ይሻሉ። ነገር ግን ከሃዲያኖች ቢጠሉትም እንኳ አሏህ ብርሃኑ ሙሉ እንዲሆኑ እንጅ አይፈቀድላቸውም።ከላይ በጠቀስኩት የኛው ሐገር ታሪክ ከሃዲያኖች ከረጅም ጊዜ ጀምረው እስካሁን ድረስ የአሏህን ብርሃን ለማጥፋት ጧት ማታ በመታገል ላይ ይገኛሉ። ይህ የአሏህ ብርሃን ኢስላም ነው፤ የመልዕክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮት ነው።
እንደሚታወቀው ድሮ የነበሩ አፄዎች ኢስላምን ለማጥፋት ያልሞከሩት ነገር አልነበረም ነገር ግን አልቻሉም። አሁን ያሉትም አፄዎች ይህን በመሞከር ላይ ይገኛሉ ሆኖም አይችሉም። ምክኒያቱም ህዝብን ማጥፋት ይቻል ይሆናል መለኮታዊ የሆነውን አስተምህሮት ግን መቼም ቢሆን ማጥፋትም ሆነ መበረዝ አይችሉምና። ትናንት 16 ሰዎች የነበሩ ሙስሊሞች ዛሬ ግማሽ ሚሊየን የሚሆኑ ሙስሊሞች ሐገራችን ላይ ይገኛሉ፤ አዎ! ሐገራችን ኢትዮጲያ ላይ። ይህ ለኢትዮጲያ ሙስሊሞችም ሆነ አለም ላይ ላሉ ሙስሊሞች ትልቅ ድል ነው። የኢስላም ብርሃን ፅልመት የወረሳቸውን የአለም ክፍሎችም ይሁን የሃገራችን ክፍሎች ሰንጥቆ የሰዎችን መለኮታዊ ፣ ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ህይወት ቀይሮ የመግባት ብርቱ ሃይል አለው።
ሁሉም ሙስሊም ኢስላም ድል ሲያደርግ ወይም ኢስላም ሲያብብ ማየት ይሻል! ነገርግን እኛ ሙስሊሞች ድልን በመመኘታችን እና ተስፋ በማድረጋችን ብቻ ድል አይመጣም! ይልቁንም ድልን ልንጎናፀፍ የምንችለው እራሳችነን ቀይረን በአሏህ መንገድ ዲኑን የበላይ ለማድረግ ስንታገል ነው።
ልኡል ሃያል የሆነው አምላካችን አሏህ እርዳታ የምናገኝበትን ፣ ድል የምንጎናፀፍበትን መንገድ ሲነግረን እሱ ከማንም እርዳታ የማይፈልግ ሆኖ ሳለ የአሏህን ሃይማኖት የበላይ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አመላከተን።
አሏሁ አዘወጀል በቁርአኑ በሱረቱ ሙሐመድ አንቀፅ 7 ላይ እንዲህ ይላል፦
=<({አል-ቁርአን 47:7-8})>=
{7} እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ብትረዱት ይረዳችኋል። መረገጫዎቻችሁንም ያጠነክርላችኋል።አሏሁ አዘወጀል በሱረቱል አንፈል አንቀፅ 39 ላይ እንዲህ ይላል።
=<({አል-ቁርአን 8:39)}>=
{39} ፊትና እስከማይኖር ድረስ ታገሏቸው።ይህ ትግል በእምነትና እና በክህደት ፣ በጭቆናና በፍትህ ፣ በነፃነት እና በባርነት ያለ ትልቅ የሆነ ሁሉን ያማከለ ትግል ነው። ሆኖም ትግሉ ማንኛውንም ሙስሊም ማህበረሰብ ያማከለ ሲሆን ሁሉም ባለው እውቀት ፣ ባለው ተሰጥኦ ፣ ባለው ጊዜ ፣ ባለው ሃብት እራሱን ሊያዘጋጅ ይገባል። ጉዞው አሰልች ቢመስልም ወይም እንደ ተራራ ገዝፎ ቢታየንም እራሳችነን በእውቀት እና በጥበብ አስታጥቀን ጉዟችነን በትዕግስት መግፋት ይኖርብናል።
ይህ ትግል ሙስሊሙን ማህበረሰብ ዳግም በማንኛውም የህይወት ዘርፍ የበላይ ማድረግ ሲሆን ትግሉ ቁርአንና ሱናን አጥብቆ በመያዝ ቅድሚያ በነፍሶቻችን ላይ መዝመት ይጠይቃል፤ አንድነትን ፣ መተጋገዝን ፣ ቅንጅትን ፣ ቆራጥነትን እና መሱአትነትንም ይፈልጋል። ሁላችነም ለዚህ ትግል እንነሳ! ስራዎቻችነን ከራሳችን እና ከቤተሰቦቻችን በመጀመር ወደ ሌላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ክፍል እንቀሳቀስ! ወጣቶች ይህን ወሳኝ የድሜያችነን ክፍል በአግባቡ እንጠቀምበት! ቡኋላ የወጣትነት ጊዜህን በምን አሳለፍከው ተብለን መጠየቃችን አይቀሬ ነውና!!!
=<({አል-ቁርአን 3:139})>=
139 ደካሞች አትሁኑ፤ አትዘኑም። በእርግጥ እውነተኛ አማኞች ከሆናችሁ የበላዮች(አሸናፊዎች) ትሆናላችሁ።የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|